ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈፀመችው የድሮንና የሚሳኤል ጥቃት በትንሹ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ በዩክሬን መዲና ኬቭና ካርኪቭ የሚሳኤልና የድሮን ጥቃት መፈጸሟ ተሰምቷል። ካርኪቭ በተፈጸመው ጥቃት በህጻናት ትምህርት ቤት በደረሰው ጉዳት ቢያንስ 27 ህጻናት መቁሰላቸው ተነግረዋል።
ዘለንስኪ አክለውም ጥቃቱ የሚያሳየው ሩሲያ ላይ በቂ ጫና እየተደረገ አለመሆኑን ነው በዚህም ጦርነቱን እንድትገፋበት አድርጓታል ብለዋል። በዩክሬን ላይ የተፈፀመው ጥቃት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፑቲን ጋር ሊያደርጉ የነበረውን ስብሰባ መሰረዛቸውን ካሳወቁ ከሰአታት በኋላ ነው።
ዶናልድ ትራምፕ ከፑቲን ጋር በቡዳፔስት እንደሚገናኙ ካሳወቁ ከቀናት በኋላ ዳግም ጥቅም ለሌለው ስብሰባ ጊዜዬን አላጠፋም ማለታቸው ተሰምቷል። ክሪሚሊን በዋሺንግተንና አውሮፓውያን መሪዎች ቀረበውን የሰላም ስምምነት አልቀበልም ማለቷም ተሰምቷል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው
የ-አብስራ ሚሊዮን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












