በቀጣዮቹ 10 ቀናት የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ ከ5 ዲግሪ ሴልሺዬስ በታች እንደሚሆን የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
ኢንስቲትዩቱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በላከው መግለጫ እንደጠቆመው፤ በሚቀጥሉት 10 ቀናት ውስጥ አልፎ አልፎ የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ ከ5 ዲግሪ ሴልሺዬስ በታች ይወርዳል። በሌላ በኩል በሚቀጥሉት 10 ቀናት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆነ አካባቢዎች ከቀላል እስከ ከባድ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል።
በተጨማሪም አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናት በሰሜን ምዕራብ እና በሰሜን የሃገሪቱ አካባቢዎች ወቅቱን ያልጠበቀ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር ተጠቁሟል።
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












