በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ ፍልስጤማዊው ጋዜጠኛ ሳሌህ አል-ጃፈራዊ በጋዛ ከተማ ግጭት ውስጥ መገደሉ ተሰማ።
በጦርነቱ በሚሠራቸው ቪዲዮዎች ታዋቂነትን ያገኘው የ28 ዓመቱ ጋዜጠኛ በጋዛ ሳብራ ሰፈር ውስጥ በነበረ ግጭት ዘገባ እየሠራ እያለ “በታጠቁ ሚሊሻ” አባላት በጥይት ተመትቶ መገደሉ ነው የተረጋገጠው ።
ፍልስጤማውያን ምንጮች እንደገለጹት እሁድ ዕለት በከተማዋ ሳብራ ሰፈር በሐማስ የፀጥታ ኃይሎች እና በዶግሙሽ ጎሳ ታጣቂዎች መካከል ግጭቶች መካሄዳቸውን አስታውቋል ። ሆኖም ግን የአካባቢው ባለሥልጣናት በጉዳዪ ዙሪያ እስከአሁን በይፋ ያሉት ነገር የለም።
የአካባቢው ባለሥልጣናት በሃመስና በእስራኤል አዲስ የተኩስ አቁም ስምምነት ቢደረስም በጋዛ ውስጥ ያለው የፀጥታ ሁኔታ አሁንም ፈታኝ መሆኑን በተደጋጋሚ ማስጠንቀቃቸውን ቀጥለዋል ሲል የዘገበው አልጀዚራ ነው።
በ ሰላማዊት ወልደገሪማ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












