አረንጓዴው – የሥራ፣ የልምላሜና የዕድገት ምልክት ነው፡፡
ቢጫው – የተስፋ፣ የፍትሕና የዕኩልነት ምልክት ነው፡፡
ቀዩ – ለነጻነትና ለዕኩልነት መስፈን የሚደረግ የመስዋዕትነትና የጀግንነት ምልክት ነው፡፡
በሠንደቅ ዓላማው ላይ የሚገኘው ዓርማ ትርጉም …
ክቡ ሰማያዊ መደብ – ሰላምን ያመለክታል፡፡
ቀጥታና ዕኩል የሆኑት መስመሮች – የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንዲሁም የሐይማኖቶችን ዕኩልነት ይገልጻል።
ኮከቡ – የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በመፈቃቀድ የመሠረቱትን አንድነት ያሳያል።
ቢጫው ጨረር – በመፈቃቀድ አንድነት ለመሠረቱት ብሔር፣ ብሔረሰቦች የፈነጠቀውን ብሩኅ ተስፋ ይወክላል።
18ኛው የሠንደቅ ዓላማ ቀን “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ይከበራል፡፡ (ኢዜአ)
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












