በርካታ እስራኤላውያን አደባባይ በመውጣት የታጋቾችን መለቀቀቅ በተስፋና በጉጉት እየጠበቁ ይገኛል፡፡
በሃማስና እስራኤል መካከል በተደረገሰው የእስረኞችና ታጋቾች ልውውጥ ስምምነት መሰረት ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ሃማስ ታጋቶችን ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በርካታ እስራኤላውያንም በቴልአቩቭ ታጋቾች አደባባይ (Hostages Square) በመሰባሰብ የታጋቶችን መለቀቅ እየተጠባበቁ ይገኛል፡፡
ሐማስ በዛሬው እለት የሚለቃቸውን የ20 ታጋቾች ስም ዝርዝር ይፋ ሲያደርግ የእስራኤል መንግስትም የፍልስጤም እስረኞች እና ከጋዛ የታሰሩ ሰዎች ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህም 1,718 የፍልስጤም እስረኞች ሊፈታ ተዘጋጅተዋል። ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) በስፍራው ጋቾችን ለማዘዋወር ተዘጋጅቶ እየጠበቀ ይገኛል ተብሏል፡፡
በእስራኤልና በሐማስ መካከል በተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት መሠረት፣ ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) የእስራኤላውያን ታጋቾችን ከጋዛ ወደ ተስማሙበት ቦታ እንዲዘዋወሩ ገለልተኛ አስታራቂ ሆኖ ይሰራል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
በ-ሰላማዊት ወልደገሪማ












