ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል ገቡ፡፡
ሪፐብሊካኑ ትራምፕ እስራኤል ከመግባታቸውም ባሻገር በመካከለኛው ምስራቅ ዘላቂነት ያለው ሰላም ለማምጣት ይሰራሉም እየተባለላቸው ነው፡፡ ፕሬዚዳንቱ ዳግም ከተመረጡ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ እስራኤልን ሲጎበኙ ነው፡፡
ሃማስ በቁጥጥሩ ስራ አድርጓቸው የነበሩ እስራኤላውያንን ፤ሰባቱን በለቀቀበት ሰዓት ነው ዶናልድ ትራምፕ ቴል አቪቭ የደረሱት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ እና ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ ለትራምፕ አቀባበል አድርገውላቸዋል ፡፡
በእስራኤል ፓርላማ ወይንም ክነሴት ንግግር ካደረጉ በኋላ ወደ ግብጽ ሻርም ኤል-ሼይክ የሚያመሩም ይሆናል ዶናልድ ትራምፕ ፡፡ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእስራኤል እና ሃማስ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ በማድረግ ቁልፍ ሚና መጫወታቸው ለሰላም ቁርጠኛ መሆናቸውን ያሳያል ሲል ዋይት ሀውስ መግለጫም ሰቷል ፡፡
ዘገባው የዋሽንግተን ፖስት ነው
በ-ቢኒያም ካሴ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












