የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በመጪው 48 ሰአታት አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሾሙ አስታወቁ።
አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሾሙ ነው የሚለው መረጃ የወጣው በሀላፊነት ላይ የነበሩት የስራ መልቀቂያ ያስገቡት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሰባስቲያን ሌኮርኑ ጋር በውይይት ስምምነት ላይ መድረስ አለመቻሉን ተከትሎ ነው።
ይህንን ተከትሎ በስልጣን ዘመናቸው ከባድ ፓለቲካዊ ቀውስ ውስጥ ይገኛሉ የሚባሉት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በመጪው 48 ሰአታት ውስጥ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስተር እንደሚሾሙ በፅህፈት ቤታቸው በኩል አስታውቀዋል።
አክለውም የቀደሙት ፕሬዝዳንት ላበረከቱት አስተዋፅኦ ማክሮን ምስጋና ማቅረባቸው ተገልጿል። በሀገሪቱ ፓለቲካዊ ቀውስን ለመፍታት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መደረግ ይገባዋል የሚል ፅኑ እምነታቸውን ሲያራምዱ ለቆዩ ተቃዋሚዎች እርምጃው አዲስ የትችት በርን ሊከፍት ይችላል ተብሏል።
የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በአውሮፓውያኑ 2017 ወደ ስልጣን ከመጡ አንስቶ ሰባት ጠቅላይ ሚኒስትሮች ተቀያይረው ያገለገሉ ሲሆን፤ በ2024 ብቻ አራት ጠቅላይ ሚኒስትሮች መቀያየራቸው ይገለፃል።
ይህም የፕሬዝዳንት ማክሮን የአንድ ሰሞን ወዳጆችና የቀድሞ አመራሮች እንዲሁ ተፎካካሪዎች ሳይቀር ትችት አሰንዝሮባቸዋል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው።
በ-የአብስራ ሚሊዮን












