ከእስራኤል ጋር ወደ መልካም ግንኙነት ለመምጣት አስቸጋሪ ነው ሲሉ የሶርያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሳድ አል ሻይባኒ ተናገሩ። እስራኤል የተከለከሉ ቀጠናዎችን እና የጎላን ተራሮችን መያዟ የአብራሃም ስምምነትን እያደናቀፈው ነው ብለዋል ውጭጉዳይ ሚኒስትሩ።
በዚህ ሰዓት እስራኤል የሶሪያን ግዛቶች እየወረረች ፣ ስለ አብርሃም ስምምነት እና መልካም ግንኙነት ማውራት አሰቸጋሪ ይሆናል ያሉት ሻባይኒ ሶሪያ ከማንም ጋር ግጭት አትፈልግም ሲሉም ገልፀዋል።
እስራኤል የ1974ቱን ስምምነት በመጣስ እና ከወታደራዊ ነፃ በሆኑ መሬቶች ጥቃት እያደረሰች ነው በሚል ወቀሰም ቀርቦባታል።
ሶሪያ ከጎረቤቶቿ ጋር እና በቀጠናው ሰላም እንዲመጣ ፍላጎት ያላት ሲሆን፣ ከአሜሪካ ጋር ስትራቴጂካዊ ትስስር በመፍጠር እንዲሁም ከአካባቢያዊ እና ዓለም አቀፍ አካላት ጋር መስራት እንደምትፈልግ ሻባይኒ ተናግረዋል።
ባለፈው ታህሳስ 2024 የብሽር አል አሳድ መንግስት ተገርስሶ የአህመድ አልሻራ መንግስት ከተመሰረተ በኋላ ሶሪያ በውስጥ እና ውጭ ሀይሎች በሚደርስ ጥቃት ለመረጋጋት ተስኗታል ይላሉ የፖለተካ ተንታኞች ።
አናዶሉ እንደዘገበው
በ-ቶማይ መኮንን












