የሩሲያ ሚግ-29 የጦር ጀቶችን ኢራን ወደ አገር ውስጥ ማስገባቷን አረጋገጠች።
የኢራን ብሄራዊ ደህንነት የፓርላማ ዓባል እና የውጭ ፖሊሲ ኮሚሽን ባለሙያ ናቸው መረጃውን ያረጋገጡት። ሚግ -29 የጦር ጀቶች በአሁኑ ሰዓት በሺራዝ አርፈዋል ብለዋል። በሩሲያ እና በኢራን መካከል ያለውን የመከላከያ ኃይል ግንኙነትም እየጠነከረ መምጣት የሚጠቁም ነው የሚል አስተያየት ተሰቷል።
የኢራንን ደህንነት ለማስጠበቅ እና የአየር ላይ መከላከል አቅሟን ለማጠናከር በረዥም ጊዜ ዕቅድ ውስጥ የተካተተው ደግሞ ኤስ ዩ-35 ጀቶችን በቅርቡ ወደ ቴህራን ማስገባት ነው። በሌላ በኩል የቻይናው ኤች ኪው-9 እና የሩሲያው ኤስ -400 የአየር መከላከያ ስርዓቶች ወደ ኢራን ይገባሉ ብለዋል ባለስልጣኑ።
እነዚህ ሁሉ በኢራን ምድር ሲሀጠሙ” ጠላት የአቅምን ቋንቋ ይረዳል” ሲሉም አሳስበዋል። ይህ ደግሞ በሩሲያና ምዕራቡ ዓለም በኩል ያለውን ውጥረት ሳይቀር መልኩን ይለውጠዋል የሚል ስጋት ተጋርጧል።
ዘገባው የ አይ ኤፍ ፒ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












