ኔፓል ለ19 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውን የማህበራዊ ሚድያዎች እገዳ አነሳች።
ኔፓፕ 26 በሚደርሱ ማህበራዊ ሚድያዎችን ማገዷ ተከትሎ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ በዜጎችና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ 19 ሰዎች ከሞቱ በኋላ ጥላው የነበረውን እገዳ አንስታለች።

በሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች ሰኞ ዕለት ወደ ካትማንዱ የፓርላማ ሕንጻ በመግባት እንደ ፌስቡክ ፣ዩቱዩብና ኢንስታግራም ጨምሮ በ26 ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ መንግስት የተጣለውን እገዳ እንዲያነሳና ሙስናን እንዲያጠፋ ጠይቀዋል።
ይህን ተቃውሞ ተከትሎም የሀገሪቱ መንግስት እገዳውን ማንሳቱን የኔፓል የመገናኛ ብዙሃን እና ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር አስታውቀዋል። ባለፈው ሳምንት የኔፓል መንግስት የማህበራዊ ሚዲያ እገዳውን ያጸደቀው የሀሰት ዜናዎችን፣ የጥላቻ ንግግርንና የኦንላይን ማጭበርበሮችን ለመከላከል በሚል ምክንያት ነበር።
ነገር ግን ሰኞ እለት ወደ ጎዳና የወጡ ወጣቶች የመንግስት አምባገነናዊ አመለካከት በመቃወም እንደሆነ ተናግረዋል። እንደ ኢንስታግራም ያሉት የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች በኔፓል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች ያሏቸው ሲሆን፤ ለ መዝናኛ፣ ለዜና እና ለንግድ ሥራ ይጠቀሙባቸዋል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው
በ ሰላማዊት ወልደገሪማ












