የኢትዮዽያ ስትሮክ ፋዉንዴሽን በአዲስ አበባ ከተማ የተሟላ የስትሮክ ሕክምና ማዕከል (comprehensive stroke service Center ) ሊገነባ መሆኑ ተገለፀ።
ማዕከሉ ተገንብቶ ስራ ሲጀምር ከአገር ወጥተዉ መታከም ለማይችሉ ታማሚዎች እና ቤተሰብ ትልቅ እፎይታ የሚሰጥ ሲሆን፣ በአፍሪካ አህጉር ደረጃ እንኳ በጣም ውስን በሆኑ አገራት ብቻ የሚሰጥ በመሆኑ እንደ አገር ለጀመርነዉ የጤና ቱሪዝምም በዉጭ ምንዛሬ ግኝት የሚኖረዉ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ጉልህ ነዉ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ለስትሮክ ሕክምና ማዕከል መገንባት መሬት ከማቅረብ ጀምሮ ሌሎች ድጋፎችን ያደርጋል ብለዋል ከንቲባዋ።
የከተማችን ነዋሪዎች ስትሮክን ጨምሮ ሌሎችም ተላላፊ ያልሆኑ ደዌዎችን አስቀድሞ መከላከያዉ መንገድ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እና ከአካባቢ ከንፅህ በመሆኑ ለዚህም ታልመዉ በተሰሩ የከተማችን የእግረኛ መንገዶች፣ የስፓርት ማዕከላት እንድትጠቀሙ ሲሉ ከንቲባ አዳነች ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ስትሮክ እና ሌሎችም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ።
መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ነው።












