አሜሪካ ፤ ብሪታኒያ እና ፈረንሳይ በኢራን ላይ ማእቀብ እንዲጣል የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን እየወተወቱ መሆናቸው ተገለጸ፡፡
E3 በመባል የሚታወቁት ሀገራት ኢራን የ2015ቱን የኑክሌር ስምምነት ጥሳለች ሲሉም ከሰዋል፡፡ ቴህራን የኑክሌር መርሀ ግብሯን በድብቅ እያሳለጠች ነው ሲሉ የሚከሱት ሶስቱ ሀገራት፤ ተመድ በ30 ቀናት ውስጥ ማዕቀብ ለመጣል የሚያስችለውን ሂደት እንዲጀምር ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
ሀገራቱ በኢራን ማዕቀብ መጣል አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት የተሰጡበት ምክንያት የፊታችን ጥቅምት በኢራን ላይ የተጣለው ማዕቀብ ስለሚያልቅ ነው ተብሏል፡፡ ባለፉት ወራት ሶስቱ ሀገራት እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት ካደረሱ በኋላ ከኢራን ባለሰልጣናት ጋር በኑክሌር ጉዳይ ቢሰበሰቡም ከመፍትሄ ላይ አልደረሱም፡፡
አሜሪካ በፈረንጆቹ 2018 በዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ዘመን ከኢራን የኑክሌር ስምምነት መውጣቷ ይታወሳል፡፡
ቲ አር ቲ እንደዘገበው
በ – ቶማይ መኮንን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












