ልበቀናው፤ አዛኙ ዳኛ የሚባሉት ዳኛ ፍራንክ ካፕሪዮ በ88 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። ዳኛ ፍራንክ ካፕሪዮ ፍርድ ቤት ላይ በሚያሳዩት ርህራሄ እውቅናን አግኝተዋል።
ዳኛ ካፕሪዮ በሙያቸው ከነበራቸው ፍትዓዊነት እና ታማኝነት ባሻገር፣ ፍርድ ቤት የመጡ ሰዎችን ታሪክ ሲሰሙ የሚያሳዩት ሰብዓዊነት ብሎም ለሰዎች ያላቸው ርህራሄ እና ትህትና የበርካቶችን ቀልብ ስበዋል።
ዳኛ ፍራንክ ካፕሪዮ “Caught in Providence” ከተሰኘው የቲቪ ፕሮግራማቸው ተቀነጫጭበው በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጩ ቪዲዮዎች በሚሊየኖች ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፈዋል።እንዲሁም ”በዓለም ላይ ምርጥ ዳኛ” አስብሏቸዋል።
ዳኛው ለረጅም ጊዜ በጣፊያ ካንሰርን ሲታገሉ መቆየታቸውን ኤ ቢ ሲ ኒውስ ዘግቧል።
ካፕሪዮ ከባለቤታቸው ጆይስ ካፕሪዮ ጋር ወደ 60 አመት ገደማ የቆዩ ሱሆን አምስት ልጆች፣ ሰባት የልጅ ልጆች እና ሁለት የልጅ ልጅ ልጆች እንዳፈሩ የኤ ቢ ሲ ኒውስ መረጃ ይጠቁማል።
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












