ሩሲያ ለህንድ የነዳጅ ዘይት መላኳን ቀጥላበታለች ሲሉ የሩሲያው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዴኒስ ማንትሮቭ ተናገሩ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተሩ ህንድ ከአራቱ የሩሲያ ዋና የንግድ አጋር አካላት አንዷ ናት ያሉ ሲሆን ፤ በነዳጅ ዘይት እንዲሁም በሌሎችም የሀይል አቅርቦቶች ላይ ያላቸውን የንግድ ትስስር ይበልጥ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
ዴኒስ ማትሮቭ ይህንን ያሉት ከህንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤስ ጃኢሻንካር ጋር በነበራቸው አመታዊ ስብሰባ ላይ ነው።
ህንድ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነትን ከሞስኮ ከፍተኛ የነዳጅ ሀይልን በመሸመት በገንዘብ ደግፉለች በሚል ከምዕራባውያኑ ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባቷ ይታወሳል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር እንዲሁ ህንድ ከድርጊቷ አልተቆጠበችም በሚል የ25 በመቶ ታሪፍ መጣላቸው ይታወሳል።
ለሶስት ቀናት ይፉዊ የስራ ጉብኝት በሞስኮ የሚገኙት የህንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃኢሻንካር በበኩላቸው ከሩሲያ ጋር በተለያዩ መስኮች ያላቸውን የንግድ ትስስር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።
ህንድና ሩሲያ ከፍተኛ የንግድ ልውውጥ ከሚያደርጉ የዓለም ሀገራት መካከል ሲሆኑ በመጪው የፈረንጆቹ 2030 ወደ 100 ቢሊየን ዶላር የንግድ ልውውጥ እንዲኖራቸው እየሰሩ መሆኑም ይገለፃል።
ዘገባው የአር ቲ ነው።
በ-የአብስራ ሚሊዮን












