ቤጂንግ በመጪው እሁድ ጃፓን የፈጸመችባትን ወረራን የሚያስታውስ እና የዓለም ፀረ-ፋሺስት ጦርነት (ሁለተኛው የዓለም ጦርነት) ድል 80ኛ ዓመትን ለማክበር ለሚደረገው ሰልፍ የመጀመሪያ ልምምዷን አድርጋለች ።
በተለቀቁ ተንቀሳቃሽ ምስሎች፤ ከተለያዩ ወታደራዊ ክፍሎች የተውጣጡ ወታደሮች በኢሉሚኔድ ቲያንማን አደባባይ ልምምዳቸውን ሲያደርጉ እንዲሁም አንድ የሙዚቃ ቡድን ስራዎቹን ሲያቀርብ፣ አርቲስቶች ሲዘፍኑ እና ሲጨፍሩ ታይቷል።
ልምምዱ 22,000 የሚደርሱ ተሳታፊዎችን ያካተተ ሲሆን እንደ አዘጋጆቹ ገለጻም ልምምዱ ስራዎችን በጥልቀት ለመገምገም እንዲሁም የመጪውን ፕሮግራም የተሳካ ለማድረግ ታቅዶ የተዘጋጀ ነው ተብሏል።
በ-ሔርሜላ ተመስገን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












