ልክ በዛሬው ቀን እ.ኤ.አ. በነሀሴ 6፣ 1945 በጃፓን ላይ ሁለቱ የኒክሌር ቦምቦች ተጥለዋል፡፡
የሂሮሺማ እና የናጋሳኪ ጥቃት በመባል በሚታወቀው በዚህ ክስተት በሂሮሺማ 140,000 ሰዎችን እና በናጋሳኪ 73,000 ሰዎችን ገድሏል ። ከተገደሉት መካከል 38,000 ያህሉ ህጻናት ነበሩ።
በቀጣዮቹ ዓመታትም የተረፉ ሰዎች ሉኪሚያ፣ ካንሰር እና ከጨረር የሚመጡ አስከፊ የጎንዮሽ ጉዳቶች ገጥሟቸው ነበር።
እ.ኤ.አ. ነሐሴ 6 ቀን 1945 በሂሮሺማ ላይ የፈነዳው የዩራኒየም ቦምብ 15,000 ቶን የሚያክል የፈንጂ ክብደት ነበረው። ከአካባቢው ከነበሩት ህንፃዎች 70 በመቶውን ያወደመ ሲሆን፣ የሙቀት መጠኑም 4,000°C ደርሶ ከፍተኛ ዝናብም ጥሎ ነበር።
በዚህ ፍንዳታ የመጀመሪያ እርዳታ ሰጪ የሆኑ ሆስፒታሎች፣ የእሳት አደጋ ሰራተኞች፣ የእርዳታ ድርጅቶች በቀላሉ አገልግሎት መስትጠት አልቻሉም ነበር። በደረሰው ጉዳት ምክንያት እርዳታ ለመስጠት የማይቻልበት ሁኔታ አስከትሎ ነበር።
በሂሮሺማ እና ናጋሳኪ አብዛኞቹ ተጎጂዎች ስቃያቸውን ለማቃለል ምንም ዓይነት እንክብካቤ ሳይደረግላቸው ህይወታቸው አልፏል። እንዲሁም ከኒክሌር ጥቃት በኋላ እርዳታ ለመስጠት ወደ ከተሞቹ ከገቡት መካከል አንዳንዶቹ በጨረር ሳቢያ ሕይወታቸው አጥተዋል።
በ-ሔርሜላ ተመስገን












