”ሃይማኖቶች ለሰላም፣ለአንድነት እና ለአብሮነት” በሚል መሪ ሃሳብ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት 4ኛው ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ በሐረር ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።
የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከሐረሪ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የሰላም ጉባዔ ”ሃይማኖቶች ለሰላም፣ለአንድነት እና ለአብሮነት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በሀገር አቀፍ ላይ 300 የሚሆኑ የሁሉም ክልልና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔና የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊዎች የሚታደሙ ሲሆን በኮንፍረንሱ ላይ ሁለት ሰነዶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ተጠቁሟል።
የጉባዔው ተሳታፊዎች በሐረሪ ክልል የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላና በክልሉ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር ፣ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ጸሓፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ጠባቂ ተወካዮች፣ ከተለያዩ ክልሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ የስራ ኃላፊዎች በጉባዔው ላይ ተገኝተዋል።
መረጃው የሀረሪ ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ነው












