እስራኤል በጋዛ እያካሄደች ያለችውን ጥቃት አጠናክሯ የቀጠለች ሲሆ፣ በደይር አል-ባላህ አከባቢ በፈጸመችው የተጠናከረ የአየርና የምድር ጥቃት ቢያንስ 65 ፍልስጤማውያን መገደላቸው የህክምና ምንጮች አረጋግጠዋል።
እስራኤል በሺዎች በሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ተፈናቃዮች በተጨናነቀው ደይር አል-ባላህ ከተማ ደቡባዊና ምስራቃዊ ክፍሎች ላይ የተጠናከረ የመሬት እና የአየር ጥቃት ጀምራለች።
እስራኤል ከጥቅምት 2023 በጋዛ ጥቃት ከጀመረች ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ታንኮቿን ወደ መካከለኛ ጋዛ ደይር አል-ባላህ አካባቢ ያስገባች ሲሆን፣ በጥቃቱም በርካታ ፍልስጤማውያን መሞታቸው ተገልጿል ።
በዚህም ትናንት የእስራኤል ጦር በደይር አል-ባላህ በከፈተው የታንክ ጥቃት መኖሪያ ቤቶችና መስጊዶች ተመተዋል። ቢያንስ ሶስት ፍልስጤማውያን ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋልም ነው የተባለው።
ይህ አዲስ ጥቃት በጋዛ ያለውን አስከፊ ሰብአዊ ቀውስ ይበልጥ እንደሚያባብስ ተሰግቷል ።
ከዚህ ጥቃት አንድ ቀን ቀደም ብሎ የእስራኤል ወታደራዊ ኃይል በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩ ፍልስጤማውያን እንዲፈናቀሉ አስገዳጅ ትእዛዝ ማውጣቱም ይታወሳል። በዚህም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ምዕራብ ወደ ሜዲትራኒያን የባህር ዳርቻ እና ወደ ደቡብ ወደ ካን ዩኒስ ለመሸሽ ተገደዋል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
በ ሰላማዊት ወልደገሪማ












