የእስራኤል ጦር በየመን ሆዴዳህ ወደብ ላይ ጥቃት የሰነዘረ ሲሆን የሁቲ መሰረተ ልማቶችን ኢላማ አድርጓል፡፡
የእስራኤል ጦር ቢያንስ 115 ፍልስጤማውያንን ከገደለ በኋላ 27 ሰዎች በዚኪም እና ሌሎች 13 ሰዎች ደግሞ ጂኤችኤፍ በሚመራው ጣቢያ የሚገኙ ነዋሪዎችን ገድሏል፡፡ በሌላ በኩል እስራኤል በጋዛ ከተማ በሚገኘው የውሃ ጣቢያ ላይ ባደረሰው ጥቃት በትንሹ አምስት ፍልስጤማውያን የተገደሉ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል።
የቴልአቪቭን ጥቃት ቱኒዝያ፣ ኢራቅ፣ ቱርክ፣ ሞሮኮና ሊባኖስ አውግዘዋል። እስራኤል በጋዛ ላይ ባካሄደችው ጦርነት በትንሹ 59,029 ሰዎች ሲሞቱ 142,135 ቆስለዋል። በ 2023 በእስራኤል ውስጥ 1,139 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ከ200 በላይ የሚሆኑት ደግሞ በምርኮ ተወስደዋል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
በሔርሜላ ተመስገን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












