የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመሰረተበትን 70ኛ አመት እና የማስተማሪያ ሪፈራል ሆስፒታሉን 100ኛ አመት ከጥር ወር ጀምሮ በተለያዩ መርሃ ግብሮች እያከበረ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲው የፊታችን ሐምሌ 12/2017 በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን ከ2 ሺህ 6መቶ በላይ ተማሪዎችን ለማስመረቅ ዝግጅት ማጠናቀቁ ተገልጿል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አስራት አፀደወይን ከጣቢያችን NBC Ethiopia ጋር በነበራቸው ቆይታ የዘንድሮውን የምርቃት ስነ ስርዓት ልዩ ለማድረግ ከነገ ሐምሌ 11 እስከ 14/2017 ድረስ የሚከናወኑ የተለያዩ መርሃ ግብሮች መኖራቸውን ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው ባለፉት 66 አመታት ከ1 መቶ 8 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስተምሮ ማስመረቁን የገለፁት ዶ/ር አስራት የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንቶች ብሎም ተመራቂ ተማሪዎች የሚሳተፉባቸው 5 መርሃ ግብሮች እንደሚካሄዱ ጠቁመዋል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲን ራስ ገዝ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።
በ– አክረም ኑርያ












