በኢራቅ በገበያ ማዕከል ላይ በደረሰ ከፍተኛ የእሳት አደጋ ቢያንስ የ61 ሰዎች ህይወት ተቀጠፈ፡፡
በቃጠሎው የሰዎች ህይወት ከማለፉም ባሻገር በርካቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ 45 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ከአደገው መውጣታቸውንም የኢራቅ መገናኝ ብዙሃን እያስነበቡ ይገኛል ፡፡ የዋሲት ግዛት ገዥ ክስተቱን አስከፊ ነው በማለት አደጋውን ገልጸውታል።
የኢራቅ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴርም በምስራቃዊ ኢራቅ በኩት ከተማ የገበያ ማዕከል ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ በርካታ ሰዎች ሰለባ መሆናቸውን አሳውቀዋል፡፡ሚኒስቴሩ በዋሲት ግዛት የገበያ ማዕከል በተከሰተው አደጋ 14 አስከሬኖች መገኘታቸውን እና 45 ሰዎችን ማዳን መቻሉንም አስታውቋል።
የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሺዓ አል-ሱዳኒ በመግለጫቸው እንዳስታወቁት የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ እሳቱ ወደተከሰተበት ቦታ በመሄድ ለማጣራት እና ዳግም እንዳይከሰት ለመከላከል እርምጃዎችን እንዲወስድ መመሪያ ሰተዋል፡፡
ዘገባው የቢቢሲ እና አልጀዚራ ነው፡፡
በ-አብርሃም ሀይሉ












