በምስጢራዊ ፕሮግራም ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ የአፍጋኒስታን ሰዎች ወደ እንግሊዝ መወሰዳቸውን የሚጠቁም ሰነድ ሾልኮ ወጣ።
የመከላከያ ሚኒስትሩ ጆን ሄሊ 4,500 የአፍጋኒስታን ሰዎች በምስጢራዊ ፕሮግራሙ መሰረት ብሪታንያ ውስጥ አሊያም በጉዞ ላይ እንደሆኑ አረጋግጠዋል፡፡ ዩናይትድ ኪንግደም በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ወደ ግዛቷ ወስዳ ለማስፈር ውጥን የያዘችበት ሰነድ መውጣቱ አነጋጋሪ ሆኗል።
ከ33,000 በላይ ሰዎች ዝርዝር ማንነት ይፋ መሆኑ ለደህንነታቸው ስጋትን የፈጠረም ነው ተብሏል። “ታሊባን የእነዚህን ሰዎች ማንነት ከለየ አደጋው በአፍጋኒስታን ምድር ሊከፋባቸው ይችላል” የደህንነት ሰዎች ስጋት ሆኗል፡፡
የብሪታንያው መከላከያ ሚኒስትር ጆን ሄይሊ ለፓርላማው እንዳስረዱት “4,500 ጫና ውስጥ የገቡ ሰዎች ወይ ብሪታንያ ገብተዋል አሊያም ጉዞ ላይ ናቸው፡፡” ይህ መርሃ ግብር በ$540 ሚሊዮን ወጭ እየተፈጸመ መሆኑንም መከላከያ ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡ ፡
በተለያዩ ምክንያቶች በሰነዱ ጭምር ሰለባ የሆኑ 16,000 ሰዎች እስከ ግንቦት ባለው ጊዜ ውስጥ በዩናይትድ ኪንግደም እንዲሰፍሩ ተደርገዋል። ታሊባን ወደ ካቡል ድጋሜ ሲመለስ የብሪታንያን ጦር ያገዙትን ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ ያደረገው ሰነድ የተለያዩ ጥያቄዎችን ከደህንነት አንጻር እያስነሳ ነው።
በ2021 በነበረው ቀውስ ድጋፍ የሰጡ ዜጎች መሆናቸው ግልጽ ቢሆንም በርካታ አወዛጋቢ ጉዳዮች ዛሬም እየወጡ ነው ተብሏል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ












