የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል እንደገለጸው በ 25 የአሜሪካ ግዛቶች ኮቪድ-19 በድጋሜ አገርሽቶል፡፡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅና ምዕራብ የአሜሪካ አከባቢዎች እየተስፋፋ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በድጋሜ በተከሰተው በዚህ ቫይረስ የተያዙ አብዛኛዎቹ ሰዎች የጸና ህመም ባያስተናግዱም አንዳንዶቹ ግን ትኩሳት፣ የጡንቻ ህመም እና ሽፍታን ጨምሮ የጉንፋን መሰል ምልክቶችን ይታይባቸዋል።
በአሜሪካ የጤና ባለሥልጣናት እንደገለጹትም በዚህ ቫይረስ በተያዙ በሽተኞች ሆስፒታሎች ላይ ከፍተኛ ጭማሪ እያዩ መሆናቸውን ተናግረዋል ። ነፍሰ ጡር ሴቶች የኮቪድ-19 ቫይረስ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው የተባለ ሲሆን ከቫይረሱ እራሳቸውን መከላከል እንዳላእባቸው ሲ ዲ ሲ ገልጾል፡፡
በ ሔርሜላ ተመስገን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












