፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር በዩኒቨርስቲዎች የሚሰጠው የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና ከዛሬ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ አስታውቋል።
የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) እንደገለጹት ፈተናው የሚሰጠው በ51 ዩኒቨርስቲዎች በተዘጋጁ 87 የፈተና ማዕከላት ነው።
በዚህ ዓመት በሚሰጠው የመውጫ ፈተና 190,787 ቅድመ መደበኛ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ እና ከዚህም ውስጥ 102 ሺ 360 ተማሪዎች ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ፈተናው በ238 የትምህርት መርሃ ግብሮች በሁሉም የፈተና መስጫ ማዕከላት በበይነ መረብ እንደሚሰጥም ዶ/ር ኤባ ጨምረው ገልጸዋል፡፡












