። ። ። ። ። ። ። ። ።
በጋዛ እና ካን ዩኒስ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ሳይቀር በደረሰ ጥቃት በዛሬው ዕለት ብቻ 28 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ ተገልጿል፡፡
በጋዛ ሰብዓዊ እርዳታዎች እንዳይደርሱ እና አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንዳይገባ በአሜሪካ የሚረዱ ኃይሎች ምክንያት ሆነዋልም ተብሏል፡፡
በጋዛ የሚገኘው የአደጋ መከላከል ኤጀንሲ አክሎም እርዳታ ሊያቀርቡ የሞከሩ ወታደሮቻችንንም እስከመግደል የደረሰ ድርጊት ነው ሲል ወቅሷል፡፡
ዓለም ዓቀፍ የቀይ መስቀል ተቋማትም ከመቼውም ጊዜ ይልቅ በአሁኑ ወቅት በጋዛ እርዳታ ማድረግ አስቸጋሪ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የሰብዓዊ እርዳታ ቀውሱ እና ጥቃቱም በደቡባዊ ጋዛ ጭምር የበረታ ሲሆን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ዜጎች ለረሃብ እና ቸነፈር እየተጋለጡ ናቸው ብሏል፡፡
የእስራኤል ጦር በበኩሉ የጦርነት ቀጣና በሆኑ ስፍራዎች ሰብዓዊ እርዳታ ማድረስ የማይታሰብ ነው ሲል አስጠንቅቋል፡፡
በጋዛ እና አካባቢው የተኩስ አቁም ስምምነት ቦታ ያጣ ሲሆን፣ የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም ሕይወታቸውን ለማትረፍ የዕለት ምግብ የሚፈልጉ ንጹሐን ዜጎችን መግደል ተቀባይነት የሌለው ድርጊት ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ዘገባው የፍራንስ 24 ነው፡፡
በ – ፍቅረሚካኤል ዘየደ












