። ። ። ። ። ። ። ። ።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስራ ሁለት ሀገራት ላይ ሙሉ ለሙሉ የጉዞ እግድ መጣላቸው ተሰምቷል።
ለብሄራዊ ደህንነት ስጋት ናቸው ያሏቸው የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ላይ ነው ሙሉ ለሙሉ የጉዞ እግድና ሰባት ሀገራት ላይ እንዲሁ የጉዞ ገደብ የጣሉት፤
ሙሉ ለሙሉ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የጉዞ እግድ ከተጣለባቸው 12 ሀገራት አፍጋኒስታን ፣ ቻድ፣ ኮንጎ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኤርትራ፣ ሀይቲ፣ ኢራን፣ ሊቢያ፣ ማይናማር፣ ሶማሊያ፣ የመንና ሱዳን ዜጎች ናቸው።
ሙሉ ለሙሉ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ከታገዱ ሀገራት ዜጎች ባሻገር ቡሩንዲ ፣ ኩባ፣ ላኦስ ፣ ሴራሊዮን ፣ ቶጎ፣ ቱርኪሚስታንና ቬንዝዌላ የጉዞ ገደብ ከተጣለባቸው ሀገራት መካከል መሆናቸውን ነጩ ቤተመንግሥት አስታውቋል።
ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቱን የሚያግደውን ፊርማ ካሰፈሩ በኋላ “የአሜሪካን ብሄራዊ ደህንነትና የህዝባቸውን ፍላጎት ለማሟላት ውሳኔ ማሳለፉቸው የግድ መሆኑን” አንስተዋል።
ትራምፕ አክለውም በህገወጥ መልኩ በአሜሪካ የተጠራቀሙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞች አሉ ብለዋል።
ከሰሞኑ በአሜሪካ ኮሎራዶ ግዛት የተፈፀመው ጥቃት ሀገራችን ላይ የተቃጣው አደገኛ ስጋት ማሳያ ነው ብለዋል።
ከነጩ ቤተመንግስት በተላለፈው የቪዲዮ መልዕክት በአሜሪካ ላይ ጥቃት ለማድረስ የሚሹ፤ ወደ ሀገራችን እንዲገቡ በጭራሽ አንፈቅድም ብለዋል።
ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው ማለትም በፈረንጆቹ 2017 ሰባት የኢስላም ሀገራት ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ዕግድ መጣላቸው ይታወሳል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው።
በ-የአብስራ ሚሊዮን












