ም/ቤቱ የ1446ኛውን የኢድ አል አድሃ በዓልን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በዓሉ የፊታችን አርብ በመላው የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ እንደሚከበር አስታውቋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼኽ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ (ዶ/ር) ምዕመኑ በዓሉን ሲያከብር በእምነቱ አስተምህሮ መሰረት ሚስኪኖችን በመርዳትና ያለንን በማካፈል ሊሆን እንደሚገባ ገልፀዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም በእስልምና አስተምህሮ የነገው የዙል ሂጃ ዘጠነኛው ቀን ትልቅ ደረጃ እንደተሰጠው በመግለፅ እለቱን በፆምና መልካም ስራዎችን በመፈፀም ሊያሳልፍ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በኢድ ሰላት ወቅት ለፀጥታ አካላት ተባባሪ በመሆን በአግባቡ ስነ ስርዓቱ አጠናቆ እንዲመለስ ጠይቀዋል።
በ – አክረም ኑርያ












