፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ወላጆች እና አሳዳጊዎች፣ ልጆቻቸውን ከጤና ችግሮች መጠበቅ ቀዳሚ ተግባራቸው ነው። ዛሬ በልጆች እና ወጣቶች ላይ እየጨመረ ስለመጣው የስኳር በሽታ ዓይነት 1 (Type 1 Diabetes) መረጃዎችን እናካፍላችሁ፤
ይህ በሽታ፣ ብዙ ጊዜ በልጅነት ወይም ወጣትነት ዕድሜ የሚከሰት ሲሆን፣ የሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓት የራሱን ኢንሱሊን የሚያመነጩ ህዋሳትን በስህተት የሚያጠፋበት የጤና ችግር ነው።
ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
ወላጆች እና አሳዳጊዎች፣ የሚከተሉትን ምልክቶች በልጆቻችሁ ላይ ካስተዋላችሁ እባክዎን ፈጥነው የህክምና ባለሙያ ያማክሩ!
ከፍተኛ የውሀ መጠማት እና በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት፤ ልጅዎ ከወትሮው በተለየ መልኩ ውሀ መጠጣት ከጀመረ እና ሽንት ቤት ብዙ ጊዜ የሚሄድ ከሆነ።
በድንገት የሚከሰት ክብደት መቀነስ:
ያለአንዳች ምክንያት ክብደቱ እየቀነሰ ከሆነ።
ያልተለመደ የረሃብ ስሜት: ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ከመጠን በላይ የመራብ ስሜት ከተፈጠረ
ድካም እና የኃይል ማጣት: ልጅዎ ሁል ጊዜ የደከመ ወይም የኃይል የሌለው መስሎ ከታየው።
የደበዘዘ እይታ: የማየት ችግር ከተፈጠረ።
የቆዳ ኢንፌክሽኖች ወይም ቁስሎች: ተደጋጋሚ የቆዳ ችግሮች ካሉ።
በሽታው ቀድሞ ሲታወቅ ህክምናው ቀላል እና ውጤታማ ይሆናል። መዘግየት ከባድ የጤና ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል።
ምንም እንኳን የስኳር በሽታ ዓይነት 1 በህይወት ዘመን የሚዘልቅ ቢሆንም፣ በትክክለኛ ህክምና እና ክትትል ካደረጉለት ፣ ወጣቶች ሙሉ እና ንቁ ህይወት መኖር ይችላሉ።
በ- ሃና ተሰማ












