። ። ። ። ። ። ። ። ።
የአሜሪካ ፌደራል ንግድ ፍርድ ቤት የዶናልድ ትራምፕን በሀገራት ላይ ከፍተኛ ታሪፍ የመጨመር እንቅስቃሴ አገደ።
መሰረቱ በማንሀንተን ያደረገው ፍርድቤቱ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስልጣናቸውን ያለአግባብ ተጠቅመዋል፤ የሀገሪቱን የንግድ ፖሊሲ በግል ፍላጎታቸው ላይ ተመስርተው በመዘወር የአሜሪካን ኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ከተዋል ብሏል ።
በተጨማሪም በቻይና፣ ካናዳና ሜክሲኮ ላይ የጨመሩት የተናጠል ከፍተኛ የታክስ ጭማሪ ማገዱ ፍርድ ቤቱ አስታውቋል።
እንዲሁም የዓለምአቀፉ የንግድ ፍርድ ቤት በነጩ ቤተመንግስት የተጠየቀውን የአስቸኳይ ጊዜ ህግ፤ ለዶናልድ ትራምፕ በሁሉም ሀገራት ላይ ታሪፍ እንዲጥሉ የአንድ ወገን ስልጣን እንደማይሰጥም ተገልጿል።
ውሳኔውን ነጩ ቤተመንግስት በምክትል ሴክሬታሪያት ሀላፊ በኩል ተቃውሞታል።
ዘገባው የዘጋርዲያን ነው።
በ-የአብስራ ሚሊዮን












