Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

በተወካዮች ምክር ቤት የተገነባው የስማርት ክፍል ተመረቀ

በተወካዮች ምክር ቤት የተገነባው የስማርት ክፍል ተመረቀ

May 28, 2025
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia

May 28, 2025


በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ የተገነባው የስማርት ክፍል ኮሚዩኒኬሽን ፕሮጀክት ተመርቋል። በምክር ቤቱ የተገነባው ስማርት ክፍል አመራር አካላት በቪድዮ ኮንፈረንስ ውይይት በማድረግ ፈጣን በሆነ ሁኔታ ውሳኔ ለመስጠት፣ ችግሮችን ለመፍታት፣ ህብረተሰቡን ለማዳመጥ የሚጠቅምና እንደ ሀገር እየገነባን ያለውን የዲሞክራሲ ስርዓት ለማጠናከር ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተገልጿል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የሰው ሀብት ልማት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) እንዳሉት፣ የቴክኖሎጂው እውቀት ከቦታ ቦታ በአግባቡ እንዲንሸራሸር ርቀትን በማሳጠር ሰዎች በብዙ ኪሎ ሜትሮች ተራርቀው ባሉበት ሀገራዊ ጉዳዮችን በጋራ ለመወያየትና ውሳኔ ለመስጠት እንዲሁም እውቀትን ለማስተላለፍ እንደሚጠቅም ገልፀዋል።

በተወካዮች ምክር ቤት የተገነባው የስማርት ክፍል ተመረቀ

አያይዘውም ቴክኖሎጂው ከኢኮኖሚ ልማት በተጨማሪም ለትምህርት ጥራት፣ በጤናው ዘርፍም የተሻለ ልምድና እውቀት ያላቸው ሀኪሞች ከሌሎች ጋር ግኝኙነት በማድረግ እውቀትና ልምዳቸውን የሚያስተላልፉበት፣ ችግሮችን የሚፈቱበት ፕላት ፎርም ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል። መሰረተ ልማቱን ተደራሽ በተደረገባቸው አካባቢዎች ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጥ አስፈላጊውን የሰው ኃይል ማሟላት፣ በፋይናንስ መደገፍ መጠቀም እንዲሁም መጠበቅና ለወደፊቱም ተደራሽ ባልተደረገባቸው አካባቢዎች ተደራሽ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ነገሪ (ዶ/ር) አስገንዝበዋል።

የኢኖኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ከቤንሻንጉል ጉምዝ ርዕሰ መዲና አሶሳ በተገነባው የስማርት ክፍል በመገኘት የምርቃ ስነ ስርዓቱን ከምክር ቤቱ ጋር በጋራ ያከናወኑ ሲሆን፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከዚህ በፊት 5 ያህል ስማርት ክፍሎችን ገንብቶ ለተቋማት ማስረከቡን አስታውሰዋል። አያይዘውም በዛሬው ዕለት በ10 የተመረጡ የፌዴራል ተቋማት፣ በ12 በክልሎች ዋና ከተማ በተለይ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ጽ/ቤትና በ2 የከተማ መስተዳደሮች በድምሩ 24 ስማርት ኮሚዩኒኬሽን ክፍሎች ተገንብተው መመረቃቸውን ጠቁመዋል።

ቴክኖሎጂው የዲጅታል ኢኮኖሚውን ለማፋጠን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ጠቁመው ፕሮጀክቱ ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ፣ ሁሉም አስፈላጊ የቴክኖሎጂ ግብአቶች የተሟሉለት፣ በአጭር ጊዜ ያለቀና የተሳካ ፕሮጀክት መሆኑን ገልፀዋል። ዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ካስቀመጣቸው ግቦች አንዱ የዲጅታል ኢኮኖሚን ማፋጠን፣ አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች ማሟላትና መገንባት በመሆኑ ከነዚህ መሰረተ ልማቶች አንዱ የሆነው የስማርት ኮሚዩኒኬሽን መሆኑንና በተለያዩ ቦታዎች የመገንባት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

የስማርት ኮሚዩኒኬሽን ክፍል ምቹ የስራ አካባቢን ከመፍጠር አንፃር የተፋጠነ፣ የተማከለ የስራ ግንኙነት እንዲፈጠር ያስችላል፣ የጀመርነው ስራ በቀጣይ እየሰፋ ይሄዳል፣ ፕሮጀክቱ ውጤታማ እንዲሆን ለተሳተፉ እንዲሁም የዐለም ባንክ ፋይናንስ በማድረጉም ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር የተከበሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ቴክኖሎጂው በኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ሚኒስትር አማካኝነት በአይ ኢ ኔትወርክ ሶልዮሽንስ መገንባቱ ተገልጿል።
(የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት)

Source: @NBCEthiopia
Via: NBC Ethiopia
ShareTweetShare
Previous Post

1445ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ)ልዩ የበዓል ዝግጅት

Next Post

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ታገዱ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
51
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ታገዱ

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ታገዱ

በበርካታ ክለቦች የሚፈለገው የኢፕስዊች ታውኑ አጥቂ ሊያም ዴላፕ ምርጫው ወደ ቼልሲ መጓዝ መሆኑን አሳወቀ

በበርካታ ክለቦች የሚፈለገው የኢፕስዊች ታውኑ አጥቂ ሊያም ዴላፕ ምርጫው ወደ ቼልሲ መጓዝ መሆኑን አሳወቀ

የግንቦት 20 ሰሞናት! _Documentary | ዶክመንታሪ 

የግንቦት 20 ሰሞናት! _Documentary | ዶክመንታሪ 

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?