May 25, 2025
የእስራኤል ጦር “ከየመን የተነወጨብኝን ሚሳዔል አከሽፍኩ” አለ። እስራኤል እንዳለችው በተወሰነ የአገሪቱ ክፍል የአደጋ መቷል ድምጽ ሰጭ ደውሎች (ሳይረን) ማስጠንቀቂያ ሰተዋል፡፡ዘ ታይምስ ኦፍ እስራኤል በእየሩሳሌም እና በዌስትባንክ እንዲሁም በሙት ባህር አካባቢ የማስጠንቀቂያ ምልክት ሰጪ ደውሎች የተጠንቀቁ መልዕክት አስተላልፈዋል ሲል ዘግቧል፡፡

እስራኤል በጋዛ የምትፈጽመውን ጥቃት እስካላቆመች “የቤን ጉሪዮን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሳይቀር ዒላማ ውስጥ ይገባል”በሚል ሁቲዎች ጥቃታቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ በቀናት ውስጥ ከአምስት በላይ ሚሳዔሎች በእስራኤል ላይ የተወነጨፉ ሲሆን አይ ዲ ኤፍ ሁሉንም አየር ላይ አክሽፊያለሁ ብሏል። የማለዳውን ጥቃት በተመለከተ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ከየመን ሁቲዎች በኩል የተባለ ነገር የለም።
ዘገባው የታይምስ ኦፍ እስራኤልና አልጀዚራ ነው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ
፨
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBC Ethiopia












