::::::::::::::::::::::::::::::::::::
የ1446ኛው የሀጅ ጉዞ ዝግጅትን አስመልክቶ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
ለሃጅ ተጓዦች በተዘጋጀው ስፍራ በተሰጠው መግለጫ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት ዋና ፕሬዝዳንት ሼኽ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚህ ቀደም በሀጅ ጉዞ ላይ ይፈጠር የነበረውን እንግልት ማስተካከያ ማድረጉን በማንሳት ምስጋና አቅርበዋል።

የዘንድሮ የሃጅ ተጓዦችን እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት ፕሬዝዳንቱ የሀጅ ጉዞ መዝናኛ ሳይሆን ትግል በመሆኑ ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሀጅ ተጓዦች ከመስገጃ ስፍራ አንስቶ የተለያዩ አስፈላጊ ዝግጅቶች ማጠናቀቁን የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ኃላፊ ለማ ያደቻ ተናግረዋል።
በ – አክረም ኑርያ












