፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሳውዲ አረቢያ ገቡ፡፡
ትራምፕ በሁለተኛው ዙር የፕሬዚዳንትነ ዘመናቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ ጉዞ ሲያደርጉ ነው፡፡
በመጀመሪያው ዙር የስልጣን ዘመናቸውም ወደ ዋይት ሀውስ እንደመጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳውዲ አረቢያን መጎብኝታቸው ይታወሳል ፡፡

የአሜሪካው ኤር ፎስረስ ዋን የፕሬዚዳንቶች መጓጓዣ ሪያድ ሲደርስም የሳውዲ አረቢያ ሮያል አየር ኃይል F-15 ተዋጊ ጀቶች ትራምፕን አጅበው ተመልክተዋል፡፡
በመካከለኛው ምስራቅ ለሶስት ቀናት የሚቆዩት ትራምፕ ከሳውዲ በተጨማሪ ኳታር እና አረብ ኤሚሬቶችን ይጎበኛሉ፡፡
በመካከለኛው ምስራቅ የአሜሪካ ቁልፍ አጋር ናቸው የሚባሉትን እስራኤልን እና ግብጽን ሳይጎበኙ በነዳጅ የበለጸጉትን አገራት መጎብኘታቸው የፖለቲካ ፍላጎታቸውን ያሳያል ተብሏል፡፡
ሪፐብሊካኑ የመካከለኛውን ምስራቅ ውጥረት ከማብረድ ይልቅ የአሜሪካን ኢኮኖሚ የሚደግፉ የኢንቨስትመንት ጉዳዮች ላይ አተኩረው ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡
ዘጋበው የዘ ዋሽግተን ፖስት ነው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ












