:::::::::::::::::::::::::::::::::::
ሶስተኛው ዓለም አቀፍ የሰላም ፣የአብሮነት እና ልማት ጉባዔ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በሰላም ግንባታ፣ በሰብዓዊ መብት ጥበቃ፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ፣ በትምህርትና ሌሎች የልማት አጀንዳዎች ዙሪያ ከዛሬ ጀምሮ ጉባዔው ይመክራል።
በተጨማሪም ጉባዔው በተባበሩት መንግስታት ዘላቂ የልማት ግቦች፣ በአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 እና በቀጣይ መስከረም በደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው የ2025 የቡድን 20 አባል አገራት የመሪዎች ጉባኤ ያተኩራል።
ጉባኤው ከቡድን 20 አባል አገራት የመሪዎች ጉባኤ አስቀድሞ የሚካሄድ ሲሆን፤ ከጉባኤው የሚወጡ ምክረ ሃሳቦች ለአባል አገራት ስብሰባ ይቀርባል።
በጉባዔው የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ ፣የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሀሙድ አሊ የሱፍን ጨምሮ በርካታ እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛል።
በ-ሰላማዊት ወልደገሪማ












