። ። ። ። ። ። ። ። ።
ከሀያ በላይ ንፁሀን ቱሪስቶች በካሽሚር መገደላቸውን ተከትሎ ህንድ በፓኪስታን ላይ ከፍተኛ እርምጃ ልትወስድ መሆኑን አስታውቃለች።
የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቪክራም ሚሲሪ ከጥቃቱ በኋላ አስቸኳይ የፀጥታ ካቢኔ ስብሰባ ስለመጠራቱም ለጋዜጠኞች ገልፀዋል።
በዚህም በአስቸኳይ ስብሰባ ህንድንና ፓኪስታንን የሚያዋስኑ ዋና ዋና ድንበሮችን ለመዝጋትና የኢንዱ ወንዝ ውሀ የማካፈል የውሀ ስምምነት ለማራዘም መወሰኑ ተናግረዋል።
አክለውም፣ ወደ ህንድ በልዩ ቪዛ የሚጓዙ ፓኪስታናውያን እንዲታገዱም የገቡትም በ48 ሰዓት ህንድን ለቀው እንዲወጡ አሳስበዋል።

የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር የህንድን እርምጃና አደጋውን ተከትሎ ማብራሪያ እንዲሰጡ በብሄራዊ ፀጥታ ኮሚቴ ጥሪ እንደቀረበላቸው ታውቋል።
ለ26 ንፁሀን ህልፈት ለበርካቶች መቁሰል ምክንያት የሆነው የካሽሚር የሽብር ጥቃት ቲ አር ኤፍ የተሰኘ አማፂ ቡድን ሀላፊነቱን ወስጃለሁ ብሏል።
ይህ ሀይል በፓኪስታን ድጋፍ ይደረግለታል ስትል ህንድ ተደጋጋሚ ክስ ታቀርባለች።
ጥቃቱንና የህንድን ምላሽ ተከትሎ ከሀገራቱ አልፎ ቀጠናው ውጥረት ውስጥ እንዳይገባ ተሰግቷል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው።
በ-የአብስራ ሚሊዮን












