። ። ። ። ። ። ። ። ።
ሩሲያ ክሪሚያን እንድትቆጣጠር ኬቭ እውቅና ባለመስጠቷ የሰላም ድርድሩን አውካለች በሚል የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዘለንስኪን ከሰሱ።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ትሩዝ በተሰኘው ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ለማብቃት ተቃርቦ ነበር ነገር ግን ዘለንስኪ አወከው ብለዋል።
የትራምፕ ምክትል ጄዲ ቫንስ በበኩላቸው፣ ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ ሁለቱ ሀገራት በአንዳንድ ግዛቶቻቸው ላይ ያላቸውን አቋም መተውና መልቀቅ ይገባቸዋል ባይ ናቸው።
ዩክሬን በበኩሏ በአውሮፓውያኑ 2014 ሩሲያ በሀይል የተቆጣጠረችውን የክሪሚያ ፔንሱላ የይገባኛል ጥያቄ ስታነሳ ከርማለች።
ደም አፉሳሽ የሆነውና ሚሊዮን ዩክሬናውያንን ለስደት የዳረገው፣ ሶስት ዓመታትን የተሻገረው ጦርነት አሁንም ሲቀጥል የሀገራቱ የተኩስ አቁም ድርድር ትግበራም እንደሰማይ ርቋል።
የክሪሚያ ሰርጥ ሩሲያ በበላይነት መቆጣጠሯን ይደግፋሉ ተብለው ከዚህ ቀደም ትራምፕ ለተነሳላቸው ጥያቄ ማንም ቢቆጣጠረው ግድ እንደሌላቸውና ጦርነት እንዲያበቃ ስለመፈለጋቸው ብቻ አንስተዋል።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ በበኩላቸው ሩሲያ ክሪሚያን እንድትቆጣጠር መፍቀድ ከህገመንግስቴ ውጪ ነው ሲሉ ይሞግታሉ።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።
በ-የአብስራ ሚሊዮን












