፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ጎንደርን መልሶ የማልማት ጥሪ በከተማ አስተዳደሩ ”ኑ ጎንደርን እንሞሽር” በሚል ሃሳብ ቀረበ።
በከተማዋ የተጀመረው የመልሶ ማልማት ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በመጪው ሚያዚያ 20 2017 ዓ.ም ይካሄዳል።
መርሃግብሩን አስመልክቶ ዛሬ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ለኢትዮጵያውያን፣ ለጎንደር ከተማ ነዋሪዎች፣ ለኢትዮጵያ ወዳጅ የሆኑ አለም አቀፍ ማህበረሰብ ኤምባሲዎች እና በመላው አለም ለሚኖሩ ሀገር ወዳጆች ጥሪ ቀርቧል።
መግለጫውን የሰጡት የጎንደር ከተማ ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው “ኑ ጎንደርን እንሞሽር” የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ጎንደርን ወደቀደመ ገናናነቷ፣ ስልጣኔዋ እና ደረጃዋን የጠበቀች ከተማ የማድረግ ውጥን ያለው መሆኑ ገልጸዋል።
ገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብሩ የፊታችን ሚያዚያ 20 2017 በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል ይካሄዳል።
በ-ቆንጂት ዘውዴ












