2-1 በተጠናቀቀው ጨዋታ ለሲቲ ጎሎቹን በርናርዶ ሲልቫ እና ማቴዮስ ኑኔስ ሲያስቆጥሩ፣ ቪላን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ጎል ማርከስ ራሽፎርድ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ አገናኝቷል።
ለቻምፒዮንስ ሊግ ስፍራ ተናንቀው የሚገኙትን ሁለቱን ቡድኖች ያገነኘው ጨዋታ በኳስ ቁጥጥር በባለሜዳው ሲቲ 62 በመቶ የበላይነት ተይዞ ነበር።
ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል በተደጋጋሚ በመድረስም ሲቲ የበላይነቱን ሲይዝ፣ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ በማድረግ ተመጣጣኝ መሆን ችለዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ 61 ነጥብ በመያዝ በጊዜያዊነት 3ተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፣አስቶን ቪላ በነበረበት 7ተኛ ላይ ቆይቷል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












