::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
በህንድ በምትተዳደረው ካሽሚር ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ 26 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ጥቃቱ በቅርብ ጊዜ ከደረሱት ሁሉ አስከፊው መሆኑን የህንድ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የካሽሚር አማፂ ቡድን በማህበራዊ ሚዲያ ባስተላለፈው መልእክት ለጥቃቱ ሃላፊነቱን ወስጃለሁ ያለ ሲሆን በግዛቷ ከ85ሺ በላይ “የውጭ ዜጎች” እንዲሰፍሩ መደረጉ ቅሬታ እንዳስነሳበት ገልጿል፡፡
ፖሊስ በቱሪስቶች ላይ በተከፈተው ተኩስ የሞቱት ሰዎች ከአንዱ በስተቀር ሁሉም የህንድ ነዋሪዎች መሆናቸውን አስታውቋል።

ከጥቃቱ በኋላ የሳዑዲ አረቢያ ይፋዊ የስራ ጉብኝታውን ያቋረጡት የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ አጥቂዎቹ ለፍርድ እንደሚቀርቡ በመግለጽ ድርጊቱን ተቃውመዋል፡፡

በህንድ እና በፓኪስታን የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባት ካሽሚር ለአስርት አመታት በዘለቀው አመፅ የሺህዎች ህይወት ቢቀጠፍም በቱሪስቶች ላይ ጥቃት ደርሶ አያቅም ነው የተባለው፡፡ ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡
በ-ለያ ክብሮም












