::::::::::::::::::::::::::::::::
ማንችስተር ዩናይትድ ትላንት ምሽት በይሮፓ ሊግ ጥሎ ማለፍ በሊዮን ከውድድሩ ውጪ ሊሆን ደቂቃዎች ሲቀሩት ድል ማድረግ ችሏል።
5-4 በሆነ ከፍተኛ የግብ መጠን የተጠናቀቀው ጨዋታ፣ ቀያይ ሰይጣኖቹ በፈረንጆቹ 1999 በኑካምፕ ባየር ሙኒክን በፍጻሜ ጨዋታ ከመመራት ተነስተው የዋንጫው አሸናፊ የነበሩበትን ምሽት አስታውሷል።

ሊዮን አሸንፎ ሊወጣ በመሰለ ጊዜ ዩናይትድ ወደ ጨዋታው መመለስ ችሏል። አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው ተጨማሪ ደቂቃዎች 3 ግቦችን በማሰቆጠር ወደ ግማሽ ፍጻሜ አልፈዋል።
አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት “ የ1999 ድራማዊ ጨዋታን ደግሜ ማየት ይኖርብኛል” በማለት ከመመራት ተነስተው ባለቀ ሰዓት ማሸነፋቸውን አድንቀዋል።
በክለቡ እና ደጋፊዋች ከቅርብ ጊዜያት በፊት ሲገፋ የነበረው ሃሪ ማግዋየር ዩናይትድን ወደ ቀጣይ ዙር ያሻገረችውን ግብ ከመረብ አገናኝቷል።
በመሃል ሜዳ ላይም ብዙ የሚወቀሰው ካሰሜሮ ነሎስ ብላንኮዎቹ ቤት የነበረውን ብቃት ያስታወሰ ምሽት አሳልፏል።
ሌላኛው የእንግሊዝ ቡድን ቶተንሃምም ሳይጠበቅ በጀርመን ፍራንክፈርትን 1-0 በማሸነፍ ወደ ቀጣይ ዙር አልፏል።
አርሰናል፣ማንችስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም በአውሮፓ ውድድሮች ወደ ግማሽ ፍጻሜ በማለፍ እንግሊዝን የሚወክሉ ቡድኖች ሆነውዋል
በ – አልፈሪድ ነስሮ












