፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፤ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ልብ የላቸውም (no hearts ) ሲሉ ወቀሱ፡፡
ጆ ባይደን ወግ አጥባቂ የትራምፕ ደጋፊዎች አሜሪካ ከዚህ በፊት በታሪኳ የማታውቀውን መከፋፋል እንዲፈጥሩ አድርገዋቸዋል ሲሉ ተናግረዋል ፡፡
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በስልጣን በቆዩበት ከፈረንጆቹ 2020 እስከ 2024 ድረስ ወግ አጥቂዊችን ሰይጣኖች በሚል በመተቸት የሚታወቁ ሲሆን አሁን ላይ አሜሪካን እየከፋፈሏት ነው ብለዋል፡፡
ከነጩ ቤተ መንግስት ከወጡ በኋላ የመጀመሪያ የተባለውን ንግግር ያደረጉት ባይደን ፤ የአሜሪካን ፌደራል ህጎች በመሻር ታሪክ እየቀሩ ነው ሲሉ ባይደን፤ ትራምፕን በነገር ሸንቆጠጥ አድርገዋቸዋል ፡፡
በሌላ በኩል የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩቢዮ የባይደን ዘመን አጀንዳዎች ተዘግተዋል ሲሉ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡ ዘገባው የአርቲ ኒውስ ነው ፡፡
በ-ቶማይ መኮንን












