፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ቻይና ከነገ ጀምሮ ገቢራዊ የሚሆን ከአሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ125 በመቶ ታሪፍ ጣለች፡፡
የቻይና እና የአሜሪካ የታሪፍ ጦርነት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን ከ34 በመቶ ወደ 84 በመቶ ታሪፏን ከፍ ያደረገችው ቤይጂንግ ፤ዛሬ ደግሞ 125 በመቶ አድርሳዋለች ፡፡
ቤይጂንግ ከዋሽንግተን ጋር የገባችበትን የታሪፍ እሰጥ አገባ አሁን ያለበት ላይ ለማቆም ብትወስንም የንግድ ጦርነቱ ግን መልኩን ለውጧል፡፡
የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግም “ የአውሮፓ ህብረት ዓባል አገራት አሜሪካን በጋራ እንቃወም” የሚል ጥሪ አቅርበዋል ፡፡
“በንግድ ጦርነት ማንም አሸናፊ አይሆንም ”ብለዋል የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ፡፡

በሌላ በኩል ቻይና ከዚህ በኋላ ከአሜሪካ ጋር የታሪፍ አጸፋዊ ምላሽ ውዝግብ አይኖረኝም ብላለች፡፡
የአሜሪካ መንግስት መደበኛ ባልሆነ መንገድ የሚጥለው ታሪፍ የዓለም አቀፉን እንዲሁም የኢኮኖሚ ህግን የሚጥስ ነው በሚል ወንጅላለች፡፡
መሰረታዊ የምጣኔ ሀብት ህግጋትንም የሚጥስ ፤አንድ ወገን የሚያደርገው ጫና ነው በሚል አሜሪካን ለመኮነን የሞከረችው ቻይና በአንዳንድ ምርቶቿ ላይ እስከ 145 በመቶ ቀረጥም ተጥሎባታል ፡፡
የቻይና የንግድ ሚኒስቴር”ታሪፍ የአሜሪካን ሌሎች ላይ ጫና የማሳደር ባህሪ ፤እና አስገዳጅነት የሚያጋልጥ እንጂ ፤በዘርፉ ላይ ትርጉም የለሽ ነው ” የሚል መግለጫ አውጥቷል፡፡ “የቁጥር ጨዋታ እና ቀልድ ነው” ብላለች ቤይጂንግ በንግድ ሚኒስቴሯ በኩል፡፡
ዘገባው የዋሽንግተን ፖስት እና የቢቢሲ ነው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ












