በ አክረም ኑርያ
NBC Ethiopia
የአማራ ክልል የሀገራዊ ምክክር ሂደት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሜዳ እየተከናወነ ይገኛል:: በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች፣ የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል የተወከሉ ተሳታፊዎች ታድመዋል።
የክልሉ የምክክር ሂደት አስተባባሪ ኮሚሽነር መላኩ ወልደማሪያም ለዘመናት በዘለቀው መጠፋፋት ከድህነትና ከኋላ ቀርነት ውጪ ምንም ያተረፍነው ነገር የለም ብለዋል ። እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ከምክክር በስተቀር ሌላ ምንም አይነት አማራጭ የለም ያሉት ኮሚሽነር መላኩ በመነጋገር አዲስ የፖለቲካ ስርዓትን መፍጠር እንደሚቻል ገልፀዋል።
ከዚህ በኋላ በየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ ጦርነት ሊቆምና ሁሉም ወደ ምክክር ሊመጣ ይገባዋል ያሉ ሲሆን ይህንን ማድረግ ከቻልን ኢትዮጵያ የአፍሪካ ፈርጥ የምትሆንበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ገልፀዋል ። በህብረት በርካታ ድሎችን ማስመዝገብ ተችሏል ያሉት ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳዬ በበኩላቸው ይህንን ምክክር እውን ማድረግ ከቻልን በአድዋ እና በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ ያገኘነውን ድል መድገም እንደሚቻል ተናግረዋል።













