
የሹዋሊድ በዓልን ምክንያት በማድረግ የአምስቱ አጎራባች ክልሎች የባህል አውደ ርዕይና ፌስቲቫል በሐረር ከተማ ተከፍቷል።
“የቅርስ ሀብቶቻችን ለቱሪዝም ልማታችን” በሚል መሪ ቃል የተከፈተውን የባህል አውደ ርዕይና ፌስቲቫሉን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የክልልና የፌደራል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በጋራ ከፍተውታል።

በባህል አውደ ርዕይና እና ፌስቲቫሉ ላይ ባህላዊ ጭፈራዎችና ውዝዋዜዎች፣ ባህላዊ የአለላ ስፌቶች፣ ባህላዊ ቁሳቁስና አልባሳት ለእይታ ቀርበዋል።የሹዋሊድ በዓል በሐረሪዎች ዘንድ በድምቀት የሚከበር የአደባባይ በዓል ሲሆን፤ በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች ይታደሙታል። በዓሉ ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በተለያዩ መርሀ ግብሮች እስከ ምሽት ድረስ በድምቀት ይከበራል።
Source:
NBC Ethiopia
Via:
@NBCEthiopia












