በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 7 አመታት የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚያሳይ የፎቶ አውደ ርዕይ በኦሮሚያ ባህል ማዕከል ተከፈተ፡፡
በኦሮሚያ ኮሚሽን ቢሮ አስተባባሪነት በተዘጋጀው የፎቶ አውደ ርዕይ በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ሴክተሮች ባለፉት አመታት የሰሩትን ስራዎች እና ያስመዘገቡትን ውጤቶች ይዘው ቀርበዋል።
በዐውደ ርዕዩ መክፈቻ ላይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፥ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ሰዓዳ አብዱራህማን፣የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ እና ሌሎች የፌዴራልና የክልሉ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
ዐውደ ርዕዩ በኦሮሚያ ክልል የተመዘገቡ ውጤቶችን እና በክልሉ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ሀብቶች የሚታይበት ነው ሲሉ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ሰዓዳ አብዱራህማን ተናግረዋል፡፡ በክልሉ የሚገኙ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ሀብቶችን በሚገባው ልክ ለማስተዋወቅም የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በ-የአብስራ ብርሃኑ












