።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ “ፊቼ ጫምባላላ” ለማክበር ከማለዳ ጀምሮም የሲዳማ ተወላጆች ባህላዊ ዜማን በማሰማት ወደ በዓል ማክበሪያ ስፍራ በማቅናት ላይ ይገኛሉ።
በአደባባይ በሚከበረው የሲዳማ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ “ፊቼ ጫምባላላ” በዓል ላይ የፌዴራል እና የክልል መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና ሌሎች እንግዶችም ይታደማሉ።
ከአስር ዓመታት በፊት “ፍቼ ጨምባላላ” በተባበሩት መንግሥታት የሳይንስ እና ባህል ድርጅት “ዩኔስኮ” ከማይዳሰሱ የሰው ልጆች ባህላዊ ሀብቶች ስር መመዝገቡ የሚታወስ ነው።
ዘገባው የኢዜአ ነው።











