።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የአውሮፓ ሀገራት ዜጎች በቂ ምግብና ውሀ ገዝተው በመጠባበቂያነት ማስቀመጥ አለባቸው ሲል የአውሮፓ ህብረት አስጠነቀቀ፡፡
የአውሮፓ ህብረት 450 ሚሊዮን ዜጎች ለአስቸኳይ ጊዜ የሚሆን ስንቅ መግዛት አለባቸው ያለው በዓለም ላይ የተፈጥ አደጋ ፤ የሳይበር ጥቃት ፤ የአየር ንብረት ለውጥ ፤ ህዝባዊ የጤና ችግር እና ጦርነት በ27ቱ የህብረቱ ሀገራት ሊከሰት ይችላል በሚል ፍርሀት ነው ተብሏል፡፡
ህብረቱ በዓለም ላይ የተፈጠረውን የሰላምና ደህንነት እጦት አስመልከቶ ዜጎች በቂ ምግብ ፤ ውሀ፤ መድሀኒት እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ጨምሮ እንዲሁም እስከ 72 ሰአት ሊቆዩ የሚችሉ ነገሮችን መያዝ ያስፈልጋል ሲል ገልጿል፡፡
እንደፖለቲካ ተንታኞች የህብረቱ ስጋት ወደፊት ሊመጣ የሚችል አደጋ መኖሩን አመላካች ነው ሲሉ ስጋታቸው አስቀምጠዋል፡፡
ኢስተርን አይ፤ ኢኮኖኖሚክ ታምስ እና ስካይ ኒውስ ዘግበውታል፡፡
በ-ቶማይ መኮንን












