።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የግብርና ማሽነሪዎች ላይ የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማምጣት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኢንቨስትመንትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) ገለጹ።
ሚኒስትር ዴኤታዋ ከቻይና የግብርና ማሽነሪ አምራቾች እና ማሽነሪ የሚገጣጥሙ የግል ኩባንያ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።

በኢትዮጵያ ከቻይና ኤምባሲ የንግድና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ካውንስለር በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል።
ውይይቱ በኢትዮጵያና ቻይና የግብርና ማሽነሪ ኢንተርፕራይዞች መካከል የቴክኖሎጂ ሽግግር ማምጣት እና የንግድ ትስስር መፍጠርን ያለመ ነው።
የግብርና ሜካናይዜሽንን አስመልክቶ ሰፊ ምክክር ተደርጓል ሲል የግብርና ሚኒስቴር በመረጃው አመልክቷል።












