።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
“ግማሹ ዓለም የቤላሩስ ዓይነት ስልት ያለው አምባገነን አስተዳደር ህልሙ ነው” አሉ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ።
“ቤላሩስ በትክክለኛ ጥንቅቅ ባለ አምባገነናዊ ክንውን ብሄራዊ ጥቅሟን እና የግዛት አንድነቱና ገንብታለች” ባይ ናቸው አንድ ለእናቱ የሚንስክ ፕሬዚዳንት ሉካሼንኮ፡፡
ግማሹ ዓለም የሚመኘው ዓይነት አምባገነንነት ይሉታል ፕሬዚዳንቱ፡፡
ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ይህን ያሉት በሰባተኛው ዙር የፕሬዚዳንትነት በዓለ ሲመታቸው ሰዓት ነው፡፡
ቤላሩስን ለሶስት አስርት ዓመታት ገደማ የመሩ ፕሬዚዳንትም ያደርጋቸዋል፡፡
ቤላሩስ ከሶቭዬት መውደቅ በኋላ ከሉካሼንኮ ውጭ ሌላ ፕሬዚዳንት አይታ ባታውቅም እሳቸው ግን በኩራት አስተዳደራቸውን ይገልጹታል፡፡
“ደስተኛው ፕሬዚዳንት እኔ ነኝ” ብለዋልም፡፡
አገሩን በሚወድ ተመሳሳይ አመለካከት ባለው ህዝብ እንደተከበቡም አሳውቀዋል፡፡
ማንም መሪ እንዲህ ዓይነት ጠንካራ ሰራተኛ እና ታማኝ ህዝብ የለውም በሚል ህዝባቸውን አሞካሽተዋል ሉካሼንኮ፡፡
ቤላሩስ በብዙ መኩራት አለባትም የሚል ሀሳባቸውን አጋርተዋል፡፡
የመናገር ነጻነትን አገራቸው በአግባቡ እየተገበረች መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡
ዴሞክራሲ ከእኛ በላይ ላሳር ከሚሉት አገራት ይልቅ እኛ ጋር አለ ብለዋል አሌክሳንደር ሉካሼንኮ።
ምዕራቡ ዓለም የአውሮፓ ብቸኛው አምባገነን ይላቸዋል ፕሬዚዳንቱን፡፡
ዘገባው የአር ቲ ነው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ












