። ። ። ። ። ። ። ። ።
የጤና ሚኒስቴር የጨቅላ ህጻናት ሞት ለመቀነስ እና የጤና ስርዓትን ለማሻሻል ከNEST360 ጋር በመተባበር በሚተገበረው ፕሮጀክት የተለያዩ የህክምና መሳሪያዎች ተረክቧል፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በNEST360 ፕሮጀክት አማካኝነት የጨቅላ ህጻናት ሞትን ለመቀነስ የሚዱ ስራዎችን እያከናወነ ሲሆን ከመደበኛው የመማር ማስተማር ሂደትን ባሻገር ጥናትና ምርምርን በመስራትና ፋይናንስን ማፈላልግን እየሰራ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በፕሮጀክት አማካኝነት 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው የጨቅላ ህጻናት የህክምና ለማድረግ የሚያችሉ የህክምና መሳሪያዎች ለጤና ሚኒስቴር አስረክቧል፡፡
በመርሃግብሩ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ድጉማ እንደ አገር የእናቶችን ብሎም የጨቅላ ህጻናት ሞትን ለመቀነስ በርካታ ስራዎች እየተስሩ መሆኑን በመግለጽ ውጤቱ ግን አጥጋቢ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

በNEST360 ፕሮጀክት አማካኝነት የጨቅላ ህጻናት ሞትን ለመቀነስ የሚረዱ 11 አይነት የክህምና መሳሪያዎች ድጋፍ መደረጉን በመጠቆም ይህም በዘርፉ የሚሰራውን ስራ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡
ድጋፉም በ5 ክልሎች በሚገኙ 16 ሆስፒታሎችና ከ290 ተቋማት አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውል መሆኑ ተገልጿል፡፡ ክልሎቹም ኦሮሚያ፣ አማራ ፣ ትግራይ፣ ሲዳማና አፋር ሲሆኑ በቀጣይም በቀሪ ክልሎች ላይ ድጋፉ ይቀጥላል ተብሏል፡፡
በተያያዘም ጤና ሚኒስቴር ጤና ሚኒስቴር ለ13ኛ ግዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የአፍና የጥርስ ጤና አጠባበቅ ቀንን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርህግብርን አከናውኗል፡፡
በ-ሰላም ይልማ












